26 July, 2025
0 Comments
1 category
<div id="page" class="site">
<a class="skip-link screen-reader-text" href="#content"><?php esc_html_e( 'Skip to content', 'your-theme-textdomain' ); ?></a>
<header id="masthead" class="site-header">
<?php get_header(); // This will pull in your theme's standard header ?>
</header><div id="content" class="site-content">
<div id="primary" class="content-area">
<main id="main" class="site-main">
<div class="page-content-wrapper">
<h1><?php the_title(); // Displays the page title created in WordPress admin ?></h1>
<p>
የአእምሮ ጤና በኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ከተነፈጋቸው እና ችላ ከተባሉ ዘርፎች አንዱ ነው።
የአእምሮ ጤና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና አጀንዳ አካል እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል፤ ነገር ግን በተጨባጭ
በአመራር ደረጃ ለጉዳዩ ኃላፊነት የወሰደው አካል ማን እንደሆነ ለማየት ያስቸግራል።
</p>
<div class="important-section">
<p><strong>በዘርፉ የምንሠራ በርካታ ባለሙያዎች የምንጠይቀው ጥያቄ አለን!!</strong></p>
<p>በጤና ሚኒስቴር ውስጥ ለአእምሮ ጤና ጉዳይ በቁምነገር የሚሠራ አካል አለ ወይ? ለአእምሮ ጤና ብቻ የተቋቋመ መምሪያ ወይም የአመራር ቡድን አለ ወይ? ምክንያቱም በተጨባጭ የምናያቸው ነገሮች በጣም አሳሳቢ ናቸው::</p>
</div>
<h2>አሳሳቢ ነጥቦች:</h2>
<ul>
<li>የአእምሮ ጤና ክፍል የሌላቸው ጤና ጣቢያዎች መኖራቸው</li>
<li>ግልጽ የአእምሮ ጤና አመራር የሌላቸው ሆስፒታሎች መኖራቸው</li>
<li>ወጥ የሆነ የመድሃኒት አቅርቦት አለመኖር</li>
<li>የተማሩ ነገር ግን ሥራ ላይ ያልዋሉ የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎች መኖራቸው</li>
<li>በዘርፉ የተቀናጀ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና አለመኖሩ</li>
<li>ራሱ የቻለ የአዕምሮ ጤና ዲፓርትመንት አለመኖሩ</li>
<li>ህክምና ያላገኙ ወይም የተዘነጉ የአእምሮ ህመምተኞች መኖራቸው</li>
</ul>
<p>
ይህ ሁኔታ በጤና ሚኒስቴር ውስጥ የኢትዮጵያን የአእምሮ ጤና ችግር በንቃት የሚከታተል እና
ለተግባራዊነቱ የሚሰራ አካል/ተቋም፣ መምሪያ ወይም ቡድን መኖሩን እንድንጠራጠር ያደርገናል።
በወረቀት ደረጃ የአእምሮ ጤና መምሪያ ቢኖርም እንኳን በሚፈለገው ደረጃ ለማኅበረሰቡ ተገቢው
አገልግሎት ከመስጠት አንፃር እንቅስቃሴ-አልባ ይመስላል። ምንም አይነት ግልጽ ሥራ፣ ግንኙነትም ሆነ
የተቀናጀ እርምጃ አይታይም።
</p>
<h2>ጠንካራ አመራር እና ግልጽ ኃላፊነት ከሌለ:</h2>
<ul>
<li>ፖሊሲዎች/መመሪያዎች/ በወረቀት ላይ ብቻ ይቀራሉ።</li>
<li>ክትትል፣ ተጠያቂነት እና የበጀት ድጋፍ አይኖርም።</li>
<li>የአእምሮ ጤና ወደ ጎን መገፋቱ ይቀጥላል።</li>
</ul>
<div class="call-to-action">
<p><strong>አስቸኳይ ምላሽ እና እርምጃ ያስፈልገናል!!</strong></p>
<p>እንደ ሀገር የአእምሮ ጤናን እየመራ ያለው ማነው? ለድጋፍ፣ ለቅንጅት ወይም ለትብብር የምናነጋግረው ማንን ነው?</p>
<p>እንደ ሀገር የአዕምሮ ጤና ዳይሬክቶሬት/ቋሚ ተጠሪ መ/ቤት/የት ነው የሚገኘው?</p>
</div>
<p>
ኢትዮጵያ ለሕዝቦቿ ጤና በእውነት የምታስብ ከሆነ፣ የአእምሮ ጤና ጉዳይ በባለቤትነት ሊያዝ እና
በግልጽ ሊመራ ይገባል ጉዳይ ነው። በምንም አይነት ሁኔታ ትኩረት ሊነፈግ ወይም ሊረሳ አይገባም።
</p>
<p style="text-align: center; font-weight: bold; font-size: 1.3em; color: #0056b3;">
አሁንም በድጋሜ እንጠይቃለን ለአእምሮ ጤና ኃላፊው ማነው?
</p>
<p class="signature">✍️Ethio Psychiatry 2/11/2017</p>
ሓሳቡ የተገኘው ከ፡https://www.linkedin.com/posts/yordanos-yihun-a08120277_%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%88%88%E1%8A%A0%E1%8A%A5%E1%88%9D%E1%88%AE-%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%98%E1%88%88%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%8B%8D-%E1%88%9B%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8A%A5%E1%88%9D%E1%88%AE-%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-activity-7348735716182425601-XKRa?utm_source=social_share_send&utm_medium=android_app&rcm=ACoAACmi2M4BR4O0dF5UKg8WmNDpORQ_Knov2qo&utm_campaign=whatsapp
</div></main></div></div>
Category: Uncategorized
